Hiwot tadesse ትባላለች በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትአትር ጥበባት ትምህርት ክፍል ትያትር ነው የተማረችው በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ በፕሮግራም አዘጋጅነት ሰርታለች።
እናስተዋውቃችሁ…
ይህች ወጣት ልባቸው የተሰበሩ ህፃናትን ልብ ለመጠገን ቆርጣ ተነስታለች ሃሳቧም ፍላጓት ብቻ ሆኖ ያልቀረ! በአራት ቀናት ውስጥ ብቻ የሶሻል ሚዲያው “ቲክ ቶክ”ን ለተቀደሰ አላማ አውላው 208,550 ብር ከ tiktok ጓደኞቿ ሰብስባለች።
እውነት ለመናገር ቲክቶክ ዋዛ ፈዛ ነገሮችን ከፍ ካለም በግል ወይም በቡድን ሰዎች እሚደንሱበት ሰፈር አድርጌ ነው እምቆጥረው።
በምትኖርበት ሃገረ አሜሪካ ሆና በ tiktok አማካኝነት በኢትዮጵያ የልብ ህሙማ ማዕከል ውስጥ ገና በጨቅላነታቸው የልብ በሽተኛ ሆነው በአቅም ማነስ ምክንያት ወረፋ እየተጠባበቁ ለሚገኙ ህፃናት ደርሳላቸዋል…
የልደት በዓል (የገና በዓል) እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ስለ ሰው ልጆች ሲል አሳልፎ የሰጠበት በመሆኑ ብዙ አማኞች የፍቅር ስጦታን በመሰጣጠት በዓሉን ያከብሩታል።
የእነ Hiwot tadesse እና ጓደኞቿም ስጦታ በጭንቅ ውስጥ ለሚገኙ ሁለት ህፃናትን ሂወት መታደግ ያስችላል የሁለቱ ህፃናት ቤተሰቦችን “ልጄ ይድንልኝ ይሆን?” ከሚል ጭንቀት ይገላግላቸዋል፣ ስለ ልጆቹ ባሰቡ ቁጥር ለሚጨነቁት ከሙያዊ እገዛቸው ባሻገር ለተለያዩ መድሃኒቶች ለመግዣ ገንዘቡ ከሌለ ምንም ማድረግ የማይቻላቸው ሃኪሞች ትልቅ እፎይታን የሰጠ የፍቅር ስጦታ ሆኗል ።
በዛሬ ዕለትም 27/04/2013 ዓም ለማዕከሉ አምባሳደር ተዋናይት መሰረት መብራቴ አማካኝነት የገንዘብ ርክክቡ ተደርጓል።
ሂወት ታደሰ እንደገለፀችው ከሆነ “ከ 10 USD ጀምሮ እስከ ከ 300 USD ድረስ ደስ እያላቸው ደጋግ እጆቻቸውን በዘረጉ ኢትይጵያውያን አማካኝነት የጀመርነውን እንቅስቃሴ አብዝተን እንቀጥላለን የተሰበሩትንም የልጆቻችንን ልቦች መጠገናችንን አናቆምም” ብላለች ።
በቅርቡም ለሜቄዶኒያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ውስጥ ሆነው እራሳቸውን መቆጣጠር ለማይችሉ ህሙማን አንድ መኪና ሙሉ ዳይፐር ሰብስበው ወደ ሃገር ቤት እንደላኩም ነግራኛለች።
“ሃምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ ለሃምሳ ሰው ጌጡ ነው” እንዲሉ አበው ሶሻል ሚዲያውን ለሰናይ አላማ እምትጠቀመውን ጀግና ወጣት ሂዊ (Hiwot tadesse) ከታች የተቀመጠውን የtiktok አካውንቷን follow በማድረግ እርሶም የዚህ የተቀደሰ አላማ ተካፋይ ይሁኑ!!

