ከእዚህ በፊት በተለያዩ በጎ አድራጎት ስራዎች ለይ ጉልህ ሚና የነበራትና ለበርካቶች ድጋፍ ስታደርግ የቆየችዋ ኗሪነቷን በሰሜን አሜሪካ ያደረገችውና ላለፉት ሦስት ዓመታት ማበራዊ ሚድያን ለሰበዓዊነት በመጠቀም
የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን መርጃ ማዕከልን በመርዳት የምትታወቀው የማዕከሉ በጎ አድራጊ ጋዜጠኛ ህይወት ታደሰ ልደቷን በማስመልከት ከማህበራዊ ሚድያ ያሰባሰባቸውን
1.2 ሚሊዬን ብር ወኪሎቿ ፣ የማዕከሉ አመራሮችና ታካሚ ህጻናት በተገኙበት ዛሬ ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ / ም ጥቁር አንበሳ ግቢ ውስጥ በሚኘው ማዕከል ውስጥ ገንዘቡን በወኪሎቿ አማካኝነት አስረከበች።
ጋዜጠኛ ህይወት ታደሰ ለልብ ማዕከሉ ብቻ እስካሁን ከ 3,000,000 ብር በላይ ድጋፍ በማድረግ 30 ልጆችን ከሞት መታደግ ችላለች።
በመጨረሻም “ሁላችንም በመቀናጀት ሶሻል ሚዲያውን ለበጎ ነገር በመጠቀም ወገኖቻችን ከችግር እንታደግ” በማለት መልዕክቷን አስተላልፋለች።
በእሷ አማካኝነት ከከባድ የልብ ህመም የዳኑት የተወሰኑት ህጻናቶችም ለጋዜጠኛ ህይወት ታደሰ የምስጋና መልዕክታቸውን እና የመልካም ልደት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ማህበራዊ ሚዲያን የምርም ለበጎ አላማ የሚጠቀሙ ሁሉ ሊመሰገኑና ሊበረታቱ ይገባልና ጋዜጠኛ ህይወት ታደሰ ተባረኪልን።
ዋልተንጉስ ዘሸገር
እንኳን ተወለድሽ ጀግኒት
መልካም ልደት

